በሀገራችን የመጀመሪያውና ብቸኛው የግል ሞርጌጅ ባንክ የሆነው ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ ከሞደርን ሪልስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ የስምምነት ውል ተፈራርሟል፡፡
ጎሕ ቤቶች ባንክ በሀገራችን የሚታየውን የቤት ችግር ከመቅረፍ አንጻር የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ከአጋር የቤት አልሚ ድርጅቶች ጋር በመሆን የመኖሪያ ቤቶችን ግንባታ ፋይናንስ በማድረግ ለደንበኞቹ የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን እድል እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ የቤት ቁጠባ አማራጮችን በመዘርጋት በረጅም ጊዜ ብድር በተመጣጣኝ ወለድ የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ባንኩ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ለበርካታ ቤት ፈላጊዎችና ቤት አልሚዎች የሚቀጣጠሩበት እና ሀሳባቸውን ከፍላጎታቸው አቀናጅተው በስኬት በዘላቂነት ለመስራት የሚገናኙበት ቦታ ሆኖ ሰንብቷል፡፡
የዚህ ስምምነት ዋና አላማም ሞድረን ሪልስቴት በመሀል ቦሌ ሸገር ሀውስ ህንፃ አካባቢ በማስገንባት ላይ ያለውን ባለ 15 ወለል ቅንጡ አፓርትመንት ፕሮጀክት በመከታተል የተለያዩ የአከፋፈል አማራጮችን በማቅረብና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ የባንኩ ደንበኞች የቤት ባለቤት ለማድረግ ታስቦ የተደረገ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ስምምነት ነው፡፡
በዚህም መሰረት ጎሕ ቤቶች ባንክ የቤት ገዥዎችን ጥቅም ከማስጠበቅና አልሚውንና ቤት ገዥውን ፍትሃዊ ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር የሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ይገኙበታል፡፡1
· ደንበኛው ከአልሚው ጋር የሚገባው ውል የደንበኛውን ጥቅም ያስጠበቀ እንዲሆን ማድረግ፣
· ክፍያው በውጭ ምንዛሬ ሳይሆን በብር እንዲሆን እና ከአካባቢው ዋጋ አንፃር እጅግ ተመጣጣኝ ሆኖ እንዲቀርብ ማድረግ፣
· ባንኩ ለፕሮጀክቱ ማስጨረሻ ብድር ለቤት ገዥው ማመቻቸት፣
· ለአልሚው ቤት ገዥው በባንኩ በኩል የሚከፍለውንና ባንኩ ለቤት ገዥው ሊሰጥ የሚችለውን ብድር ቀጥታ ለፕሮጀክቱ ብቻ እንዲውል ባንኩ ጥብቅ ክትትል ማድረግ፣
· ግንባታው በ2 ዓመት ካልተጠናቀቀ ባንኩ ፕሮጀክቱን ተረክቦ ግንባታ ማከናወን ይገኙበታል፡፡
ስለሆነም ለነገ ቤትዎ ቁጠባዎን ዛሬውኑ በባንካችን ይጀምሩ የሚልዎት ጎሕ ቤቶች ባንክ የዚህ ቅንጡ አፓርትመንት ቤት ባለቤት ለመሆን ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤትና በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በመቅረብ ዝርዝር መረጃ ማግኘትና መመዝገብ የሚቻል መሆኑን ይገልፃል፡፡
በተጨማሪም ሌሎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን በቀጣይ የምንገልጽ መሆኑን እያሳወቅን ከቤት ማልማት ባሻገር የልጆች የቤት ቁጠባ፣ የአዋቂዎች የቤት ቁጠባ እና ሌሎች በርካታ መደበኛ የባንክ አገልግሎቶችን ከባንካችን ያግኙ ይለዎታል ጎሕ ቤቶች ባንክ፡፡
ለበለጠ መረጃዎ በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ በዝርዝር መረዳት እና የባንኩን የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመቀላቀል በእየለቱ አዳዲስ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጎሕ ቤቶች ባንክ
የትውልዱ ባንክ !
M | T | W | T | F | S | S |
---|---|---|---|---|---|---|
1 | 2 | 3 | 4 | 5 | ||
6 | 7 | 8 | 9 | 10 | 11 | 12 |
13 | 14 | 15 | 16 | 17 | 18 | 19 |
20 | 21 | 22 | 23 | 24 | 25 | 26 |
27 | 28 | 29 | 30 | 31 |