ጎሕ ቤቶች ባንክ በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ተጨማሪ ቅርንጫፉን በመክፈት ሥራ አስጀምሯል፡፡ ባንኩ ወደ ሥራ ከገባበት ከጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የቅርንጫፎችን ብዛት ስምንት ማድረስ ችሏል፣
ጎሕ ቤቶች ባንክ እስከ 30 ዓመት የሚከፈል የቤት መግዣ፣ መስሪያና ማደሻ የሚውል ብድር በተመጣጠነ የወለድ ምጣኔ እየሰጠ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ከአጋር ሪል እስቴት ኩባንያዎች ጋር በመተባበር በመጀመሪያው ዙር በመሀል አዲስ አበባ፤ ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከ በ2850 ሜትር ስኴር ቦታ ላይ ያረፈ፣ በርካታ ቤቶች ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል!
ስለሆነም በባንኩ ሒሳብ ከፍቶ የቤቱን ግምት 30 በመቶ እና ከዚያም በላይ አስቀድሞ በመቆጠብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ይሁኑ፣
ከዚህ ባለፈም ባንኩ የመደበኛ ቁጠባ፣ የጊዜ ገደብ ቁጠባ፣ የንግድ ቁጠባ፣ የሃዋላ አገልግሎት፣ የዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎቶች እና ሌሎች በርካታ የቁጠባ ዓይነቶች እየሰጠ ይገኛል፡፡
ስለ አገልግሎቱ ይበልጥ ለመረዳት ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኛው ዋና መ/ቤት ወይም በቦሌ ፣ በለቡ ፣ በሲኤምሲ፣በአራት ኪሎ፣ በድሬ ዳዋ፣ በባህር ዳር፣ በአዳማ እና በሃዋሳ ቅርንጫፎች ጎራ በማለት ማግኘት ይችላሉ።
የጎሕ ቤቶች ባንክን ማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃዎችንም ያግኙ፡፡
☞ቅርንጫፎቻችንን ያግኙ፡ https://bit.ly/3jnsTZP
ጎሕ ቤቶች ባንክ
የትውልዱ ባንክ