Goh Betoch Bank

Bank of the Generation!                              SWIFT CODE: GOBTETAA

ለጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የተደረገ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የተደረገ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. ሁለተኛ ዓመታዊ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 15 ቀን 2016
ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ አዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ በመሆኑ ባለአክሲዮኖች ከላይ
በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ተገኝታችሁ በጉባኤው እንድትሳተፉ በንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013
አንቀፅ 366(1) እና በባንኩ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 8(1) መሠረት የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት
ጥሪውን ያቀርባል፡

የባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ በብር፡ 2,127,963,000.00
የባንኩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ በብር፡ 1,373,431,000.00
የባንኩ የምዝገባ ቁጥር፡ MT/AA/3/0052524/2013
የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፡- አ.አ. ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 2፣ የቤት ቁጥር አዲስ፤

የሁለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ፣
  2. አዳዲስ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ፣
  3. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የዳይሬክተሮች ቦርድን ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ውሳኔ ማሳለፍ፣
  4. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የሂሳብ ዘመን ሪፖርት ማዳመጥና ውሳኔ
    ማሳለፍ፣
  5. እ.ኤ.አ. በ2022/2023 የሂሳብ ዘመን የተጣራ ትርፍ አመዳደብ እና አከፋፈል ላይ ውሳኔ ማሳለፍ፣
  6. የባንኩ የውጪ ኦዲተሮችን መሾም እና የሥራ ዋጋቸውን መወሰን፣
  7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን፣
  8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ማዳመጥና የዳይሬክተሮች
    ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፣
  9. የስብሰባዉን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፡፡

ማሳሳቢያ

  1. በጉባኤዉ ላይ የሚሳተፉ ባለአክሲዮኖች ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ
    መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዘዉ
    መቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2. በጉባኤዉ ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ
    ሕዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ቦሌ ጃፓን ኢምባሲ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋና መ/ቤት ወይም በሁሉም
    የባንኩ ቅርንጫፎች ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀዉን የውክልና መስጫ ቅፅ መፈረም ወይም በጉባኤዉ
    ለመካፈል የሚያስችል የውክልና ሥልጣን ለተወካይ መስጠት ይችላሉ፡፡ ተወካይም ወካዩ (ባለአክሲዮኑ)
    ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ የነዋሪነት
    መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ቅጂ እና የውክልና ሥልጣን ማስረጃዉን ዋና እና አንድ ቅጂ
    ይዘዉ በመቅረብ በጉባኤዉ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

የጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ.
የዳይሬክተሮች ቦርድ